የቡልቡላ – አላጌ – ባራ – ሚቶ መንገድ ግንባታ እየተፋጠነ ነው ።

39 ኪሎ ሜትር ርዝመትን የሚሸፍነው የቡልቡላ – አላጌ – ባራ – ሚቶ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ 46 በመቶ ስራው ተጠናቋል።

ግንባታውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው ኪቢሽ የተባለ ሀገር በቀል የስራ ተቋራጭ ሲሆን ፣ United Consulting Engineers plc ( UNICON ) ደግሞ የማማከር እና የቁጥጥር ስራውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ለፕሮጀክቱ የተመደበው 878,514,732.42 (ስምንት መቶ ሰባ ስምንት ሚሊዮን አምስት መቶ አስራ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ ሁለት ብር ከአርባ ሁለት ሳንቲም) በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው።

ከቡልቡላ ዋና ከተማ 2 . 5 ኪ . ሜ ርቀት ላይ መነሻውን ያደረገው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት የኦሮምያን ክልል ከደቡብ ክልል ጋር ያስተሳስራል። አካባቢው እንደ በቆሎ ፣ ስንዴ ፣ ቦሎቄና በርበሬ ያሉ የተለያዩ የግብርና ምርቶች የሚመረቱበት መሆኑ የመንገዱን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ጉልህ ያደርገዋል።

በአሁኑ ወቅት የመንገዱ 31 ኪ . ሜ ወይም 81 በመቶ የሰብ ቤዝ ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን ፣ 33 ኪ . ሜ ወይም 85 በመቶ የሰብ ግሬድ ስራውም ተከናውኗል። ከዚህም ባሻገር የስላብና ፓይፕ ካልቨርት ስራዎችም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ ። በቅርቡም የአስፋልት ንጣፍ ስራም እንደሚጀመር ታውቋል ።

አጠቃላይ የመንገዱ አፈፃፀም በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ፣ በተገቢው ጥራትና ጊዜ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስፈላጊውን ቁጥጥር እና ድጋፍ ያደርጋል።